“ጎንደር የኢትዮጵያ አንድነት እና የሉዓላዊነት አርማ ኾና ዘልቃለች” አማኑኤል ፈረደ (ዶ.ር)

0
ጎንደር: ግንቦት 18/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በጎንደር ከተማ የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል።
በድጋፍ ሰልፉ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የአሥተዳደር ዘርፍ አሥተባባሪ አማኑኤል ፈረደ (ዶ.ር) ጎንደር የታሪክ፣ የቀደምት ሥልጣኔ፣ የጀግንነት ማማ እና የታሪክ ማህደር መኾኗን ገልጸዋል።
“ጎንደር የዘመናዊት ኢትዮጵያ የአንድነት እና የሉዓላዊነት አርማ ኾና ዘልቃለች” ብለዋል። የዛሬው የሕዝብ ድጋፍም ይህንኑ የሚያሳይ ስለመኾኑ ነው የተናገሩት።
ብልጽግና ፓርቲ ሥልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ ዘርፈ ብዙ ስኬቶችን አስመዝግቧል ብለዋል። ለዚህም በጎንደር ከተማ የተከናወኑት በርካታ የልማት ሥራዎች ማሳያዎች መኾናቸውን አንስተዋል።
የመንገድ መሠረተ ልማቶች፣ የኮሪደር ልማት፣ የወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ፣ የፋሲል ግቢ ጥገና፣ የመገጭ ግድብ ግንባታ እና ሌሎችም የብልጽግና የልማት ውጤቶች ስለመኾናቸው ጠቁመዋል።
ብልጽግና ፓርቲ የጀመራቸውን ታላላቅ የልማት ሥራዎች አጠናክሮ እንደሚያስቀጥልም ገልጸዋል። ለፓርቲው አጋርነታቸውን ላሳዩት የጎንደር ከተማ ሕዝብም ምስጋና አቅርበዋል።
የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው ብልጽግና ፓርቲ ከምሥረታው ጀምሮ ኢትዮጵያን ከገባችበት ውስብስብ ፈተና በመታደግ የለውጥ ብርሃን ያሳየ መኾኑን ተናግረዋል። ለዚህ ጎንደር ምስክር ናት ብለዋል።
አሁንም በርካታ የልማት ጥያቄዎች እንዳሉ በመገንዘብ በቀጣይ ጠንካራ ተግባራትን እንሠራለን ነው ያሉት።
ጎንደር እንደ ቀደምት ታሪኳ ሀገር የማጽናት ኀላፊነት ያለባት መኾኑን በመገንዘብ ሕዝቡ ላሳየው ድጋፍም ምስጋና አቅርበዋል።
ዘጋቢ:- አሰፋ ልጥገበው
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
Previous article“ብልጽግና ፓርቲ ደብረታቦር ከተማን ወደ ሚመጥናት ከፍታ ለማድረስ ይሠራል” አቶ ሲሳይ ዳምጤ
Next articleምርጫ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም አማራጭ የሌለው ሕገ መንግሥታዊ ግዴታ ነው።