ምርጫው ሰላማዊ እና ፍትሐዊ ኾኖ እንዲጠናቀቅ ሁሉም ኀላፊነቱን ሊወጣ ይገባል።

20

 

ጎንደር: ግንቦት 18/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ብልጽግና ፓርቲ የድጋፍ ሰልፍ እና የምረጡኝ ቅስቀሳ በአይከል ከተማ አካሂዷል።

‎በመድረኩ የተገኙት የአማራ ክልል ሴቶች ወጣቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኀላፊ ብርቱካን ሲሳይ ‎ብልጽግና ፓርቲ የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየሠራ መኾኑን አንስተዋል።

ፓርቲው ወጣቶች በኢኮኖሚ እና በዲጂታል ቴክኖሎጂ ብቁ እንዲኾኑ መሥራቱን አንስተው ተግባሩ ቀጣይ መኾኑንም ተናግረዋል።
‎
‎ብልጽግና ፓርቲ ባለፉት አምስት ዓመታት በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካ እና በማኅበራዊ ዘርፍ ስኬት ላይ መድረሱን የማዕከላዊ ጎንደር ዞን አሥተዳዳሪ አወቀ አስፈሬ ገልጸዋል።
‎
‎ፓርቲው ያለፉት ስኬቶችን መሠረት በማድረግ ለወደፊት ጉዞው በጽናት ከሕዝብ ጋር እንደሚሠራም አስገንዝበዋል።
‎
‎ብልጽግና የዜጎች የሥራ ባሕል እንዲያድግ ስለመሥራቱ የተናገሩት አቶ አወቀ አስፈሬ ለዚህ ማሳያ ደግሞ የኮሪደር ልማት እንደኾነ ጠቅሰዋል።
‎
‎ብልጽግና ፓርቲ የሚናገረውን የሚተገብር እና የጀመረውን የሚጨርስ ፓርቲ ስለመኾኑም አብራርተዋል።
‎
‎ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ እና ፍትሐዊ ኾኖ እንዲጠናቀቅ ሁሉም ኀላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባም አቶ አወቀ መልዕክት አስተላልፈዋል።
‎
‎በድጋፍ ሰልፉ ላይ የተሳተፉ የአካባቢው ነዋሪዎች ይወክለናል ያሉትን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ መዘጋጀታቸውንም ተናግረዋል።
‎
ዘጋቢ፦‎ደስታ ካሣ
‎
‎#አሚኮ_ዜና #የብልጽግና_ፓርቲ_የድጋፍ_ሰልፍ #ጎንደር_አይከል #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous articleየድምፅ መስጫ ካርዶች ሕትመት ተጠናቆ ስርጭት ተጀመረ።
Next article“ብልጽግና ፓርቲ ደብረታቦር ከተማን ወደ ሚመጥናት ከፍታ ለማድረስ ይሠራል” አቶ ሲሳይ ዳምጤ