“የሀገራችን ዕድገት እና ልማት ባለቤቶች እኛ በመኾናችን የእኛን ምርጫ ማንም አይመርጥልንም” አሕመዲን መሐመድ (ዶ.ር)

5

 

ደብረ ብርሃን: ግንቦት 18/2018 ዓ.ም (አሚኮ) “ኢትዮጵያ ወደ ተምሳሌት ሀገር” በሚል መሪ መልዕክት የብልጽግና ፓርቲ የድጋፍ ሰልፍ እና የምረጡኝ ቅስቀሳ በደብረ ብርሃን ከተማ አካሂዷል፡፡

በመድረኩ ላይ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተሞች ልማት ዘርፍ አስተባባሪ አሕመዲን መሐመድ (ዶ.ር) ፓርቲው የጀመረውን የኢንዱስትሪ ልማት በተግባር እያሳየ መኾኑን ገልጸዋል።

ፓርቲው እየሠራቸው ያሉ የኢትዮ ኮደርስ፣ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ እና የመሶብ አገልግሎቶች ሀገሪቱ ወደ ዲጂታል እንድትሸጋገር ያለውን ጽኑ አቋም ማሳያ መኾናቸውን ጠቅሰዋል።

ይህ ስኬት የተመዘገበው ከሕዝብ ጋር በጽናት በመቆም እንደኾነም አብራርተዋል።

“የሀገራችን ዕድገት እና ልማት ባለቤቶች እኛ በመኾናችን የእኛን ምርጫ ማንም አይመርጥልንም” ሲሉ ዶክተር አሕመዲን አጽንኦት ሰጥተዋል።

ትላንት የጎደለውን ሞልቶ የበለጸገች እና ዲጂታል ኢትዮጵያን ለመገንባት በትብብር መሥራት እንደሚጠይቅም ጠቁመዋል።

የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ በድሉ ውብሸት የፓርቲው ትልቁ መመሪያ የመደመር እሳቤ መኾኑን ገልጸዋል።

ብልጽግና ስህተቶችን በማረም ኢትዮጵያን በጽኑ መሠረት ላይ ማቆም እና አካታች ዕድገትን ማረጋገጥ ዋነኛ ዓላማው መኾኑንም አስገንዝበዋል።

ፓርቲው ብዝኀ ኢኮኖሚን በመገንባት ሀገሪቱን ከውጭ ጫና ነፃ የኾነ ኢኮኖሚ ባለቤት እያደረጋት እንደሚገኝም ገልጸዋል።

ባለፉት አምስት ዓመታት በኢንዱስትሪ እና በግብርና ዘርፎች ተጨባጭ የለውጥ ውጤቶች መመዝገባቸውንም ጠቁመዋል።

ዘጋቢ፦ ለዓለም ለይኩን

#አሚኮ #የብልጽግና_ፓርቲ_የድጋፍ_ሰልፍ #ደብረ_ብርሃን #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ🇪🇹

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous articleምርጫ የሥልጡን ሕዝብ መገለጫ ነው።
Next article“የኢድ አል ዓደሃ (አረፋ) በዓል የሰላም፣ የፍቅር እና የአንድነት በዓል ነው”