ምርጫ የሥልጡን ሕዝብ መገለጫ ነው።

4
ደብረ ማርቆስ: ግንቦት 18/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በደብረ ማርቆስ ከተማ “ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር” በሚል መሪ መልዕክት የብልጽግና ፓርቲን የሚደግፍ ሰልፍ ተካሂዷል።
የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ጽሕፈት ቤት ኀላፊ እና በደብረ ማርቆስ ምርጫ ክልል የክልል ምክር ቤት እጩ ዳንኤል ደሳለኝ ብልጽግና ፓርቲ በፈተና ውስጥ ኾኖ ታላላቅ የልማት አሻራዎችን እያሳረፈ የሚገኝ ፓርቲ ነው ብለዋል። ዛሬ ከተጋን ነገን እናተርፋለን፤ ዛሬ ከተስማማን ነገን ብሩህ እናደርጋለን ነው ያሉት።
የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ተሾመ ዋለ ሕዝቡ ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ እንዲካሄድ እያደረገ ያለው ተሳትፎ አበረታች መኾኑን ገልጸዋል።
“ምርጫ የሥልጡን ሕዝብ መገለጫ እና ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር ማረጋገጫ መሣሪያ ነው” ብለዋል።
በድጋፍ ሰልፉ ላይ አሚኮ ያነጋገራቸው የከተማው ነዋሪዎች ምርጫ ለሀገር ግንባታ እና ለአስተማማኝ ሥርዓተ መንግሥት ግንባታ ወሳኝ መኾኑን ገልጸዋል።
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
Previous article“ብልጽግና ፓርቲ የባሕር በር ጥያቄያችን ዕውን እንዲኾን አበክሮ ይሠራል” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ
Next article“የሀገራችን ዕድገት እና ልማት ባለቤቶች እኛ በመኾናችን የእኛን ምርጫ ማንም አይመርጥልንም” አሕመዲን መሐመድ (ዶ.ር)