
ባሕር ዳር: ግንቦት 18/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በባሕር ዳር ከተማ “ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር” በሚል መሪ መልዕክት የብልጽግና ፓርቲ የምረጡኝ ቅስቀሳ እና የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው ብልጽግና ፓርቲ የሕዝብን የለውጥ ፍላጎት ለማሳካት እና “ሀገርን ወደ ከፍታ ለማሻገር እየሠራ ያለ ፓርቲ ነው” ብለዋል።
ብልጽግና ፓርቲ ውስብስብ ችግሮችን በጥበብ በመወጣት ሀገርን ያዳነ ፓርቲ እንደኾነም ገልጸዋል።
ሰላም እና ልማትን በማረጋገጥ ሀገርን ከድህነት እና ኋላ ቀርነት ለማውጣት እየተጋ ያለ ፓርቲ ስለመኾኑም አንስተዋል።
ፓርቲው ባለፉት ዓመታት ቃሉን በመጠበቅ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት መቻሉንም አስታውሰዋል።
ለዚህ ማሳያው ባሕር ዳርን ለነዋሪዎቿ እና ለጎብኝዎቿ እንድትመች ለማድረግ ሠርቷል፤ እየሠራም ይገኛል ነው ያሉት።
አሚኮ በሰልፉ ላይ ያነጋገራቸው የፓርቲው ደጋፊዎች የፓርቲውን የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ፕሮግራም በመደገፍ ሰልፉ ላይ መገኘታቸውን ተናግረዋል።
በተለይም የተጀመሩ የልማት እና የሰላም ሥራዎች ከግብ እንዲደርሱ በማሰብ በድጋፍ ለመግለጽ መውጣታቸውን አንስተዋል።
ምርጫው ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና ተአማኒ እንዲኾን የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱም ተናግረዋል።
ዘጋቢ፦ ቴዎድሮስ ደሴ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
