
ጎንደር: ግንቦት 18/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የብልጽግና ፓርቲ የድጋፍ ሰልፍ እና የምርጫ ቅስቀሳ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን አይከል ከተማ ተካሂዷል።
በድጋፍ ሰልፉ እና በምርጫ ቅስቀሳው ላይ የፓርቲው ደጋፊዎች፣ የአማራ ክልል ሴቶች፣ ወጣቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኀላፊ ብርቱካን ሲሳይ፣ የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አወቀ አስፈሬ፣ የዞን እና የወረዳ ከፍተኛ መሪዎች ተገኝተዋል።
በሰልፉ የነባሩ ጭልጋ ወረዳ፣ የጭልጋ ወረዳ እና የአይከል ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ደጋፊዎች የተለያዩ መፈክሮችን በመያዝ ድጋፋቸውን ገልጸዋል።
ዘጋቢ፦ደሰታ ካሣ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
