“ብልጽግና ፓርቲ የሕዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሠራ ነው” አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)

4
ደሴ: ግንቦት 18/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የብልጽግና ፓርቲ የድጋፍ ሰልፍ እና የምርጫ ቅስቀሳ በደሴ ከተማ አሥተዳደር ተካሂዷል።
የደሴ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ሳሙኤል ሞላልኝ ምርጫው ሰላማዊ ዴሞክራሲያዊ እና ፍትሐዊ ኾኖ እንዲጠናቀቅ ማኅበረሰቡ የበኩሉን እንዲወጣ አሳስበዋል።
ብልጽግና ዛሬን ከነገ ለማስተሳሰር፣ አንድነትን ለመፍጠር ይሠራል ብለዋል። በኮሪደር ልማት፣ በሕዳሴ ግድብ ግንባታ፣ በትላልቅ ፕሮጀክቶች የሀገርን ዕድገት ለማረጋገጥ መሥራቱንም ገልጸዋል።
የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) ብልጽግና ኅብረ ብሔራዊነትን የሚያጠናክር ፓርቲ ነው ብለዋል።
ወጣቶች የነገ ሀገር ተረካቢዎች ናችሁ ያሉት ምክትል ርእሰ መሥተዳድሩ ወጣቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ ፓርቲው እየሠራ እንደሚገኝ አሰገንዝበዋል።
ብልጽግና ፓርቲ የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ እና የሀገርን ከፍታ ለማረጋገጥ እየሠራ እንደሚገኝም ገልጸዋል።
ብልጽግና የሀገርን ኢኮኖሚ ለማሳደግ እና የሕዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይበልጥ እንደሚሠራም ገልጸዋል።
ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
Previous articleበባሕር ዳር ከተማ የብልጽግና ፓርቲ የምረጡኝ ቅስቀሳ እና የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
Next articleየብልጽግና ፓርቲ የድጋፍ ሰልፍ እና የምርጫ ቅስቀሳ በአይከል ከተማ ተካሄደ።