
ባሕር ዳር: ግንቦት 18/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በባሕር ዳር ከተማ የብልጽግና ፓርቲ እጩዎች፣ ደጋፊዎች እና አባላት በተገኙበት የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ይገኛል።
በምረጡኝ ቅስቀሳው የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ እና ሌሎችም ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
በድጋፍ ሰልፉ ላይ የባሕር በር ጥያቄ የብልጽግና ፓርቲ ቁልፍ አጀንዳ ነው፤ ብልጽግና ፓርቲ ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን ይገነባል እና በዓለም መድረክ የተከበረች ኢትዮጵያን እንገነባለን የሚሉ መልዕክቶች እየተላለፉ ነው።
ዘጋቢ፦ ቴዎድሮስ ደሴ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
