ባሕር ዳር ከተማ በልማት ጎዳና ላይ የምታሳየው መነቃቃት የነገ ተስፋን በተጨባጭ የሚያሳይ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ተናገሩ።

3

 

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የተፈጥሮ እውነት ከታሪክ ክብር ጋር በተዋሃደባት፣ በጣና ሐይቅና በዓባይ ወንዝ በታጀበችው የውበት ማማዋ ባሕር ዳር ገብተናል ብለዋል በማኅበራዊ ትስስር ገጻው ባወጡት መረጃ።

ባሕር ዳር ከተማ በልማት ጎዳና ላይ የምታሳየው መነቃቃት የነገ ተስፋን በተጨባጭ የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል።

ባሕር ዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ስንደርስ፣ ፍቅርና አክብሮት በተሞላበት ሁኔታ ለተደረገልን ደማቅ አቀባበል ለአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር፣ ለክልሉና ለከተማዋ ከፍተኛ አመራሮች፣ በጸሎትና በምርቃታቸው ላልተለዩን የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም ለመላው የባሕር ዳር ሕዝብ ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን አቀርባለሁ ብለዋል።

Previous articleበዳባት ወረዳ እና በዳባት ከተማ አሥተዳደር ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ወጭ የተደረገባቸው ፕሮጀክቶች ተመረቁ።
Next articleአሚኮ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ራሳቸውን እንዲያስተዋውቁ እኩል ዕድል ሰጥቷል።