
ባሕር ዳር: ግንቦት 17/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በደቡብ ጎንደር ዞን በስማዳ ወረዳ በወገዳ ከተማ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ አስመልክቶ የብልጽግና ፓርቲ ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ አካሂዷል።
በድጋፍ ሰልፉ የተገኙት የደቡብ ጎንደር ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኀላፊ መሠረት በላይ ብልጽግና የትልልቅ ሀሳቦች ባለቤት እና ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ለማሻገር እየተጋ ያለ ፓርቲ ነው ብለዋል።
በፈተናም ውስጥ ኾኖ መንግሥት ለመመሥረት እና ሀገርን ለማሻገር 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለማካሄድ ሥራዎች እየተሠሩ መኾኑን ገልጸዋል።
ኀላፊው ሕዝቡ ከፓርቲው ጎን በመቆም ምርጫው ሰላማዊ፣ ዲሞክራሲያዊ እና ተአማኒ እንዲኾን እንዲሠራም ጠይቀዋል።
መላው ሕዝብ ለምርጫው ውጤታማነት አጋዥ እንዲኾንም አሳስበዋል።
በድጋፍ ሰልፉ የሥራ ኀላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የመንግሥት ሠራተኞች፣ የከተማው ነዋሪዎች፣ የባጃጅ አሽከርካሪዎች፣ ወጣቶች እና ልዩ ልዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
