“ምርጫ ላይ የነቃ ተሳትፎ ማድረግ በዴሞክራሲ ብቻ የሚያምን ትውልድ ለመፍጠር ያግዛል” መምህራን

6
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 17/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ሕገ መንግሥቱ የሰጣቸውን መብት ተጠቅመው ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር የዝቋላ ወረዳ መምህራን ተናግረዋል።
የመራጮች ካርድ ቀድመው መውሰዳቸውን የተናገሩት መምህራኑ “ምርጫ ላይ የነቃ ተሳትፎ ማድረግ በዴሞክራሲ የሚያምን ትውልድ ለመፍጠር ያግዛል” ብለዋል።
መምህር መንግሥት መልካሙ እና እየሩስ ሰሰን ፍትሐዊ እና ተአማኒ ምርጫ ለማካሄድ በሚደረገው ጥረት ኀላፊነትን መወጣት እንደሚገባ አንስተዋል።
ሌላኛው በዋግ ዊከ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርእሰ መምህር የኾኑት በሪሁን አቤው ሁሉንም አሳታፊ የኾነ ምርጫ ማካሄድ ዜጎች የሚያምኑበት መንግሥት ለመመስረት የሚያስችል ዴሞክራሲያዊ አካሄድ ነው ብለዋል።
ምርጫ ሕዝብን እና ሀገርን የሚያሥተዳድር መንግሥት ወደ ሥልጣን የሚመጣበት ወሳኝ ምዕራፍ እንደኾነም ገልጸዋል።
ዘጋቢ፦ ሙላት ክንፉ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
Previous articleምርጫው ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና ተአማኒ እንዲኾን የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል።