🗳️​በባሕር ዳር ከተማ የወጣቶች የጎዳና ላይ የምርጫ ቅስቀሳ ተካሄደ።

7

 

ባሕር ዳር: ግንቦት 15/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ በማስመልከት የወጣቶች የጎዳና ላይ የእግር ጉዞ የምረጡኝ ቅስቀሳ አካሂዷል። በመርሐ ግብሩ ላይ ወጣቶች እና የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል።

የከተማ አሥተዳደሩ ሴቶች፣ ወጣቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኅላፊ ሰብለ ዘውዱ ወጣቱ ትውልድ ነገ ሀገርን የመረከብ ትልቅ ታሪካዊ ኀላፊነት ያለበት መኾኑን ገልጸዋል። “በሀገሪቱ የተጀመሩ ትልልቅ የልማት ፕሮጀክቶችን አጠናክሮ ለማስቀጠል ብልጽግናን መምረጥ ‘ራሳችንን መምረጥ ነው'” ብለዋል።

​ወጣቶች የፓርቲውን እሳቤ በአግባቡ በመረዳት ለቅስቀሳው በነቂስ በመውጣታቸው እና ላሳዩት ከፍተኛ ተነሳሽነት የላቀ ምሥጋና አቅርበዋል። ብልጽግና ከወጣቶች ጋር በመኾን የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ሲሠራ መቆየቱንም አውስተዋል።

​ይህ የተጀመረው የንቅናቄ እና የቅስቀሳ ሥራ ሳይገታ መቀጠል እንዳለበት ያሳሰቡት ኅላፊዋ ወጣቶች ብልጽግናን ራሳቸው ከመምረጥ ባለፈ ሌሎች እንዲመርጡም የበኩላቸውን ጥረት ማድረግ እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል። የነገዋ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንድትኾን ወጣቱ ኀላፊነቱን እንዲወጣም ጥሪ አቅርበዋል።

​ተወዳዳሪዎች ክልሉን እና ሀገርን በብቃት ማሻገር የሚችሉ፣ ማኅበረሰቡን በታታሪነት እና በታማኝነት የሚወክሉ፣ በፈታኝ ወቅት ሀገርን እና ክልሉን የታደጉ እና ቀጣይነቱንም የሚያረጋግጡ ዕጩ ተወዳዳሪዎች ስለመኾናቸው አስተዋውቀዋል።

​በምርጫው ወቅት ለእነዚህ እጩዎች ትልቅ ቦታ ሊሰጣቸው እና ወጣቱ ድምጽ ሊኾናቸው እንደሚገባ ነው ያስረዱት።

በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ወጣቱ ድምጽ የመስጠት መብቱን ከመጠቀም ጎን ለጎን የሀገርን ሰላም የማጽናት ኀላፊነቱን እንዲወጣም አስገንዝበዋል።
​
ዘጋቢ፦ሥራውድንቅ ደሳለው

#አሚኮ_ዜና #7ኛው_ጠቅላላምርጫ #ባሕር_ዳር #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous article“ቃላችንን ጠብቀን ዛሬን በአግባቡ እየሠራን፣ ነገንም አሰላስለን እየተለምን ነው” አቶ ፍስሐ ደሳለኝ
Next article👨‍👩‍👧‍👦 የቤተሰብ እሴቶች መሸርሸር ለማኅበራዊ ቀውሶች አንዱ ምክንያት ነው። 🇪🇹