
ወልድያ: ግንቦት 15/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ወሎ ዞን በቆቦ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል።
በድጋፍ ሰልፉ ላይ የተገኙት የሰሜን ወሎ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ከድር ሙስጠፋ ምርጫ የወደፊት የሀገራችንን እጣ ፈንታ የምንወስንበት እና ለሀራችን የዴሞክራሲ ግምባታ መሠረት የምንጥልበት ነው ብለዋል።
ምርጫው ባለፉት ሁለት ዓመታት ሥልጣንን በጉልበት ለመያዝ የሚደረግ ጉዞን ለማስቀረት የሚደረግ ጉዞ መኾኑንም ገልጸዋል።
የሰሜን ወሎ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አራጌ ይመር ብልጽግና ለሕዝብ ተጨባጭ ውጤት እያዝመዘገበ ያለ የሀገር እና የሕዝብ ባለውለታ ፓርቲ ነው ብለዋል።
ወጣቶችን እና ሴቶችን በማብቃት በኢኮኖሚ፣ በማኅበራዊ እና በፖለቲካ ተሳትፏቸውን ለማሳደግ ብልጽግና ሠርቷል ወደፊትም ይሠራል ብለዋል።
የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኀላፊ መንገሻ ፈንታው (ዶ.ር) ብልጽግና ፓርቲ በተለይ የራያ ቆቦን ሕዝብ በገጸ ምድር እና በከርሰ ምድር ውኃ ግብርናውን እንዲያዘምን አድርጓል ነው ያሉት።
በሀገር አቀፍ ደረጃ በገበታ ለሀገር እና በገበታ ለትውልድ ቱሪዝሙን ያዘመነ ፓርቲ መኾኑንም ጠቅሰዋል።
ብልጽግናን መምረጥ ከልማት ባሻገር አካታችነትን፣ ወንደማማችነትን፣ ኅብረብሄራዊነትን እና ዘላቂ ሰላምን መምረጥ አንደኾነም ገልጸዋል።
የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኀላፊ ፍስሀ ደሳለኝ “ባለፈው ሀገራዊ ምርጫ ቃል የገባናቸውን ፈጽመን የሰባተኛው ምርጫ እቅዶቻችንን ይዘን ነው የቀረብነው” ብለዋል።
ቃላችንን ጠብቀን ዛሬን በአግባቡ እየሠራን፣ ነገንም አሰላስለን እየተለምን በመኾኑ ብልጽግናን መምረጥ ሀገርን ማስቀጠል ነው ብለዋል።
የአደረጃጀት ዘርፍ ኀላፊው ለዛሬ ለእኛ እና ለነገ ለልጆቻችን የምትበጅ ሀገር ለመገንባት እና የቀጣይ ጉዟችንን ለማስቀጠል ብልጽግናን መምረጥ ይገባል ብለዋል።
#አሚኮ_ዜና #7ኛው_ጠቅላላምርጫ #ሰሜንወሎ_ቆቦ #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
