የኔቶ የሆርሙዝ ወሽመጥን ደኅንነት የማስጠበቅ ሐሳብ በፈረንሳይ ውድቅ ተደረገ።

11
ባሕር ዳር: ግንቦት 14/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ፈረንሳይ በሆርሙዝ ወሽመጥ የደህንነት ጥበቃ ላይ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ተሳትፎ ሙሉ በሙሉ ውድቅ አድርጋለች።
የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፓስካል ኮንፋቭረክስ በስትራቴጂካዊው የውኃ ላይ መስመር የኔቶን ጣልቃ ገብነት ፓሪስ እንደምትቃወም ገልጸዋል።
ቃል አቀባዩ እንዳሉት የሰሜን አትላንቲክ ስምምነት የተቋቋመው ለሰሜን አትላንቲክ ብቻ ነው። በመኾኑም ኅብረቱ ለመካከለኛው ምሥራቅ ጉዳይ ትክክለኛው አካል አይደለም ብለዋል።
ፈረንሳይ ተቃውሞዋን ያሰማችው የኔቶ የአውሮፓ ከፍተኛ አዛዥ ጄኔራል አሌክሰስ ግሪንኬዊች ኅብረቱ በወሽመጡ የባሕር ደኅንነት ላይ ስላለው ተሳትፎ እያሰበበት መኾኑን ከተናገሩ በኋላ ነው።
ፈረንሳይ የሆርሙዝ የባሕር ላይ ጉዞን በሰላማዊ መንገድ ለማስከበር በተቋቋመው ባለብዙ ወገን ተልዕኮ ውስጥ ያላትን ቁርጠኝነት አረጋግጣለች።
በስማቸው አጥናፍ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
Previous articleለጸናች ሀገር የወጣቶች ተሳትፎ የጎላ ነው።
Next articleበምርጫው ዕለት መምረጥ የሚያስችለንን በቂ ግንዛቤ አግኝተናል።