
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 14/2018 ዓ.ም (አሚኮ) “በላቀ የወጣቶች ተሳትፎ፤ ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!” በሚል መሪ ሃሳብ በሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ ወጣቶች የብልጽግና ፓርቲ የድጋፍ ሰልፍ አካሂደዋል።
በሰልፉ ላይ የተሳተፉት ወጣቶች የሀገርን ልማትና አንድነት የሚያጠናክሩ የተለያዩ ወቅታዊና ሀገራዊ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል። ለተጀመሩ የብልፅግና ጉዞዎች ስኬት የበኩላቸውን ሚና ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
መረጃው የእንሳሮ ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ነው ።
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ !
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
