“7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ትላንትን የምናክምበት፣ ለነገ መሰረት የምንጥልበት እና የኢትዮጲያን የብልጽግና ጉዞ የምናጸናበት ነው” ዲያቆን ተስፈው ባታብል

9
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 14/2018 ዓ.ም (አሚኮ) 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ በማስመልከት በላሊበላ ከተማ ብልጽግና ፓርቲን የሚደግፍ የአደባባይ ሕዝባዊ ሰልፍ ተካሂዷል።
የላስታ ወረዳና የላሊበላ ከተማ አሥተዳደር አንድ ላይ በመሆን ”ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር” በሚል መሪ ቃል ነው የድጋፍ ሰልፍ እና የምርጫ ቅስቀሳው የተካሄደው።
በድጋፍ ሰልፉ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ዲያቆን ተስፋው ባታብል የአንድ ሀገር ሁለንተናዊ ብልጽግና የሚረጋገጠው በምርጫ እና ከሕዝብ በተሰጠ ድምጽ ላይ የተመሰረተ ሥረዓተ መንግሥት ሲኖር ነው ብለዋል።
7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ትላንትን የምናክምበት፣ ለነገ መሠረት የምንጥልበት እና የኢትዮጲያን የብልጽግና ጉዞ የምናጸናበት ነው ሲሉም ተናግረዋል።
7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ፍጹም ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና ታዓማኒነት ያለው ኾኖ እንዲጠናቀቀ የሕዝቡ ድርሻ ከፍተኛ መኾኑንም አስገንዝበዋል።
ብልጽግና ፓርቲ የሕዝብን ክብርና ልዕልና የሚያስጠብቁ፣ ኢኮኖማሚያዊ ሉዓላዊነትን የሚያረጋግጡ እና አፍሪካዊት ኃያል ኢትዮጵያን ለመገንባት የለውጥ ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
Previous articleየደብረ ማርቆስ ከተማ ወጣቶች ለብልጽግና ፓርቲ ያላቸዉን ድጋፍ በአደባባይ እየገለፁ ነዉ።
Next articleአርሶ አደሮች ጭምር በንቃት የተሳተፉበት የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ በአንዳቤት!