ሀሰተኛ መረጃዎች በምርጫ ሂደት ምን ያስከትላሉ?

1

 

ባሕር ዳር: ግንቦት 10/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በምርጫ ወቅት የሚሰራጩ የሀሰተኛ መረጃዎች በምርጫ ሂደት ላይ ጫና ያሳድራሉ። መራጮች ሚፈልጉትን አካል በነፃነት እንዳይመርጡ እና የተሳሳተ ውሳኔ እንዲያስተላልፉ ያደርጋል፡፡

የምርጫ ውጤት ተቀባይነት በማሳጣት ለድህረ ምርጫ ሁከት ምክንያት ሊኾኑም ይችላሉ፡፡

በዕጩዎች ላይ የሚሰራጩ የስም ማጥፋት ዘመቻዎችም ፍትሐዊ የውድድር መንፈስን ይገድላሉ፡፡

በአማራ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ የዕውነታ ማጣራት አሠልጣኝ አብነት ቢኾነኝ በምርጫ ወቅት መረጃዎች በማሳሳት፣ በማዛባት ወይም በመበከል ሊሰራጩ ይችላሉ።

በዚህም የምርጫ አሥፈጻሚ አካላት፣ የዴሞክራሲ እና የሚዲያ ተቋማት ያላቸውን ተአማኒነት እንዲሸረሸር በማድረግ በምርጫ ሂደት ላይ ጥርጣሬ እንዲፈጠር ምክኒያት ይኾናል።

👉እንዴት መከላከል ይቻላል?

#የሚዲያ አጠቃቀም እና የመረጃ ግንዛቤን ማሳደግ

#መረጃዎችን ከመቀበል እና ከማጋራት በፊት የመረጃውን ትክክለኛነት ከምንጩ ማጣራት

#በማኅበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ መረጃዎችን ከታወቁ የሚዲያ ተቋማት ጋር በማነጻጸር

#የመረጃ ማጣሪያ የቴክኖሎጂ መተግበሪያ መንገዶችን መጠቀም

#በሰው ሠራሽ አስተውሎት (ኤአይ) የተሠሩ ምስሎችን እና ቪዲዮዎችን ለመለየት የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም

#በምርጫ ወቅት የሚለቀቁ ሀሰተኛ መረጃዎች የምርጫ ሂደቱን ሊያደናቅፉ እንደሚችሉ በመገንዘብ መረጃን በማጣራት ሁሉም የበኩሉን መወጣትም ይኖርበታል።

ዘጋቢ:- አሰፋ ልጥገበው

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous article#ኢትዮጵያ
Next articleየመረጃ ሉዓላዊነት 🇪🇹 ኢትዮጵያ በራሷ መረጃ ላይ ተመስርታ እንድትወስን አስችሏታል።