
ደብረ ብርሀን : ግንቦት 9/2018ዓ.ም (አሚኮ) የደብረ ብርሀን ከተማ አስተዳደር መጪውን 7ኛ ጠቅላላ ምርጫ አስመልክቶ የአደባባይ ላይ የስፖርት የምርጫ ቅስቀሳ አካሄደ።
በመርሃ ግብሩ ላይ ከሁሉም ክፍለ ከተማ የተውጣጡ ማህበረሰብ ክፍሎችና በርካታ ወጣቶች በንቃት ተሳትፈዋል።
የከተማዋ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት በስነ ምግባር የታነጸና የበለጸገ ወጣት ለመፍጠር ስፖርት ከፍተኛ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።
አቶ በድሉ አክለውም በከተማዋ የሚገኙ የቴኳንዶ እና ሌሎች ስፖርታዊ ተቋማት እያከናወኑ ያሉት ተግባር የሚበረታታ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶችን ታሳቢ ያደረጉ በርካታ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱንም ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው አስታውሰዋል።
ፓርቲው በቀጣይም የሀገሪቱን ሁለንተናዊ ብልጽግና አጠናክሮ ለማስቀጠል በትኩረት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።
ከፖለቲካው ጎን ለጎን ጤንነቱ የተጠበቀና በሁሉም መስክ የነቃ ማህበረሰብ ለመፍጠር በትጋት እንደሚሰራም ተገልጿል።
የተካሄደው የአደባባይ ላይ መርሃ ግብር የምርጫ ቅስቀሳውን ከማደመቅ ባለፈ ስፖርት ለሰላም ያለውን ሚና ያሳየ ነበር ተብሏል።
ስንታየሁ ሀይሉ
