“የገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ አስተማማኝ ኢኮኖሚን ለመገንባት በጀመርነው የብልጽግና ጉዞ ተደማሪ እመርታ ነው።” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ‎

5

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 08/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ ምዕራፍ አንድ ግንባታ ተጠናቆ መመረቅ፤ አስተማማኝ እና ጠንካራ ኢኮኖሚን ለመገንባት በጀመርነው የብልጽግና ጉዞ ተደማሪ እመርታ ነው። በመዲናችን በአጠቃላይ በ93.9 ሄክታር መሬት ላይ ከሚያርፈው የፓርኩ ስፋት ውስጥ የመጀመሪያው ምዕራፍ በ43 ሄክታር መሬት ላይ ተገንብቶ ዛሬ ተመርቋል፤ ይህም ለመካከለኛ እና ከፍተኛ ኢንተርፕራይዞች ምቹ የንግድ ከባቢ ከመፍጠር ባሻገር በሺዎች ለሚቆጠሩ ወጣቶቻችን የሥራ ዕድል ይከፍታል።

‎ፓርኩ የሀገራችን አምራቾች አቅማቸውን በማጎልበት፣ ምርታማነታቸውን ማሳደግና ተወዳዳሪነታቸውን በመጨመር ለከተማችን፣ ለሀገራችንና ለቀጣናው የሚተርፉበት ታላቅ እድልን ይዟል። በሌላ በኩል ተተኪ ምርቶችን በማምረት በአምራቾችና በሸማቾች መካከል ቀጥተኛና ቀልጣፋ የንግድ ትስስር ሲፈጥር፣ ምርቶችን ደግሞ ለውጭ ገበያ በማቅረብ የሀገራችንን የውጭ ምንዛሬ ለማሳደግ ጉልህ ሚና ይጫወታል።

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous article🏭 ጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ ዳግም ስኳር ማምረት ጀመረ።
Next articleየ30 ዓመቱ ናፍቆት ተፈታ፣ ለደብረ ማርቆስ ከተማ ዳግም ልደት ኾነ!