ብልጽግና ፓርቲ በተግባር የታዩ የልማት ለውጦችን አስመዝግቧል።

2

 

ባሕር ዳር: ግንቦት 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫን አስመልክቶ ከንግዱ ማኅበረሰብ ጋር የንቅናቄ መድረክ አካሂዷል።

የባሕርዳር ከተማ አሥተዳዳር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኅላፊ ሞላ ሁሴን ብልጽግና ፓርቲ ባለፉት ዓመታት ተጨባጭ እና በተግባር የታዩ የልማት ለውጦችን ማስመዝገብ መቻሉን ገልጸዋል። ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ እንዲኾን የንግዱ ማኅበረስብ መሥራት ይገባዋል ነው ያሉት።

ፓርቲው ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ያቀረባቸው ዕጩዎች የከተማዋን የልማት ከፍታ እና የማኅበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ አስተዋጽኦ ያበረከቱ መኾናቸውንም አንስተዋል።
ከተማዋን የማልማት ሥራ ሲከናወን የንግዱ ማኅበረሰብ የድርሻውን እየተወጣ እንደሚገኝ አንስተዋል።

በቀጣይም የተጀመሩ የልማት ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉም የንግዱ ማኅበረሰብ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ጥሪ ቀርቧል።

የውይይቱ ተሳታፊዎችም የንግዱ ማኅበረሰብ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በንቃት በመሳተፍ የዜግነት መብቱን ለመጠቀም ካርድ በእጁ አድርጎ ዝግጁ መኾኑን ተናግረዋል።

ሰላማዊ ምርጫ አለማድረግ የንግዱን ማኅበረሰብ ኢኮኖሚ የሚጎዳ ነው፤ ሰላምን ለማጽናት ግንባር ቀደም መኾን ይገባል ነው ያሉት።

የንግዱ ማኅበረሰብ በያዘው የምርጫ ካርድ የሚበጀውን ፓርቲ ለመምረጥ ዝግጁ መኾን እንደሚገባውም አስገንዝበዋል። ምርጫው ሰላማዊ እና ፍትሐዊ እንዲኾንም በመተባበር መሥራት ያስፈልጋል ብለዋል።

ተሻለ የዕድገት እና የልማት ጉዞ ያላት ሀገር ለመገንባት በመተባባር መሥራት እንደሚገባም ተገልጿል።

ዘጋቢ፦ ሥራውድንቅ ደሳለው

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous article“አባቶች መካሪ፤ ልጆች ተመካሪ ኾነን ምርጫውን በስኬት ማጠናቀቅ አለብን” የሀገር ሽማግሌዎች
Next article🌾”ብልጽግና ሀገሪቱን ከተረጅነት ወደ ረጅነት እያሸጋገረ ያለ ፓርቲ ነው” ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)