
ሰላማዊ ምርጫ ደግሞ ለሀገር መረጋጋት፣ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ እና ለሕጋዊ የሥልጣን ሽግግር መሠረታዊ ነገር ነው።
በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ትምህርት ክፍል መምህሩ አበራ ታደሰ ሕዝቡ በሚካሄደው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ በንቃት መሳተፉ የዴሞክራሲ ሥርዓት ልምምድን ያሳድጋል ብለዋል።
እንደ አማራ ክልል በጸጥታ ችግር ውስጥ ለቆየ ደግሞ ገጽታውን በመቀየር ረገድ ከፍተኛ ድርሻ አለው ነው ያሉት።
ምርጫው የዴሞክራሲያዊ ባሕል ዕድገት የሚታይበት ነውም ብለዋል። ሕዝቡ ያለበት የጸጥታ ችግር ሳይገድበው በምርጫው ንቁ ተሳትፎ ማድረጉ የተሻለ የዴሞክራሲ ባሕል እየተዳበረ መኾኑን ያሳያል ነው ያሉት።
ይህም ሕዝቡ በሕግ እና በሥርዓት የሚያምን መኾኑን የሚያረጋግጥ ትልቅ አመላካች እንደኾነም ነው የገለጹት።
ምርጫ የሕዝብ የሥልጣን ባለቤትነት የሚረጋገጥበት መድረክ ነው ብለዋል መምህሩ።
ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ማካሄድ ዜጎች በመተማመን ላይ የተመሠረተ መንግሥት እንዲመሠርቱ ያስችላቸዋል ነው ያሉት።
በነጻነት የሚሰጥ ድምፅ የዴሞክራሲ ጉልበት ነው ያሉት መምህሩ የዴሞክራሲ ሥርዓት የሚጠነክረው እና ትርጉም የሚኖረው የዜጎች ንቁ ተሳትፎ ሲታከልበት መኾኑን ጠቁመዋል።
የዴሞክራሲ መብትዎ በእርስዎ እጅ በመኾኑ ለምርጫው ሰላማዊነትም የሁሉም ድርሻ ወሳኝ ነው ብለዋል።
ዘጋቢ፦ ሥራውድንቅ ደሳለው
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
See le
