ፓርቲው የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ በማሳደግ ረገድ በተጨባጭ እየሠራ ነው።

4

 

ደብረታቦር፡ ግንቦት 05/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በደቡብ ጎንደር ዞን አሥተዳደር ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ አስመልክቶ ብልጽግና ፓርቲ ከዞኑ እና ከፋርጣ ወረዳ ሴት የመንግሥት ሠራተኞች ጋር የምርጫ ምልክት ትውውቅ እና የምረጡኝ ቅስቀሳ መርሐ-ግብር አካሂዷል።

በመድረኩ የተገኙት የአማራ ክልል ንግድ እና ገበያ ልማት ቢሮ ኀላፊ ኢብራሂም ሙሐመድ (ዶ.ር) ሴቶች በመንግሥት ግንባታ እና ትውልድን በማነጽ ረገድ ያላቸው ድርሻ የላቀ መኾኑን ገልጸዋል።

ለሀገር ግንባታ በትኩረት እየሠራ ያለውን ብልጽግና ፓርቲንም እንዲመርጡ ጥሪ አቅርበዋል።

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ጥላሁን ደጀኔ በመድረኩ እንደገለጹት ብልጽግና ፓርቲ የዘመናት የፖለቲካ ስብራቶችን በመጠገን፣ እንደ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ያሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን በማከናወን ሀገሪቱን በለውጥ እምርታ ላይ እያቆያት ይገኛል።

በመኾኑም በምርጫው ሂደት ሴቶች የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡም ጠይቀዋል።

የዞኑ ሴቶች፣ ወጣቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኀላፊ አንጓች ፋሲካው ፓርቲው የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ በማሳደግ ረገድ በተጨባጭ እየሠራ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል።

ሴቶች ለምርጫው ስኬታማነት ድርብርብ ኀላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባም አሳስበዋል።

የመድረኩ ተሳታፊ ወይዘሮ ታገኝ እንግዳአየሁ በበኩላቸው ሴቶች ከመምረጥ ባለፈ በእጩነት ጭምር በንቃት እየተሳተፉ መኾኑን ገልጸው ምርጫው ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡም አረጋግጠዋል።

#አሚኮ #ዜና #7ኛው_ምርጫ #ደብረታቦር #ኢትዮጵያ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous articleየፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ የነበራቸውን ቆይታ አጠናቅቀው ተመለሱ።
Next article“ዴሞክራሲያዊ አካሄድን ከምንጊዜውም በላይ ለማጽናት በሚያስችል የምርጫ ዋዜማ ላይ ነን” ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር)