የሳይበር ደኅንነትን ማረጋገጥ የግል ዳታን ከመጠበቅ ይጀምራል።

6
አዲስ አበባ: ግንቦት 05/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ኮሙዩኒኬሽን ባለሥልጣን የግል ዳታ አጠባበቅ አዋጅን ወደ ተግባር ለማስገባት የሚያስችሉ ሥራዎችን እየሠራ መኾኑን አስታውቋል።
ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ የግል ዳታ ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 1321/2016 ዓ.ም የወጣውን አተገባበር አስመክቶ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሂዷል።
ኢትዮጵያ የሳይበር ደኅንነትን ለመጠበቅ የዲጂታል ቴክኖሎጂውን ዘርፍ እያሳደገች ትገኛለች።
የግል ዳታ ማለት የግለሰብ ማንነትን እና ዝርዝር መረጃዎችን ከግለሰቡ ቁጥጥር ውጭ ኾኖ በሌሎች እጅ እንዳይገባ የሳይበር ደኅንነት ጥበቃ ማድረግ መኾኑን የተናገሩት የኢትዮጵያ ኮሙዩኒኬሽ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተሩ ኢንጂነር ባልቻ ሬባ ናቸው።
ያልተፈቀደ የግል ዳታ ተደራሽነት፤ መረጃን ያለአግበብ መጠቀም፤ የሳይበር ክስተቶች፣ ደካማ የተቋማት ጥበቃዎች እና የግንዛቤ ውስንነቶች ዜጎችን ለሕግ ጥሰቶች ዳርገዋል ብለዋል። አዋጁ ይህንን ለመከላከል ያስችላልም ነው ያሉት ዳይሬክተሩ።
አዋጁ የግል መረጃን ለሚሠበሥቡ እና ለሚያቀናጁ ተቋማት ግዴታዎችን የሚያስቀምጥ ሲኾን ሕጋዊነት፣ ግልጽነት፣ ተጠያቂነት፣ የዓላማ ገደብን እና ደኅንነትን የሚደነግግ መኾኑንም ጠቅሰዋል።
ዘጋቢ፦ አየለ መስፍን
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
Previous article“ጋሸና እና አካባቢው ከብልጽግና ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ተጠቃሚ ይኾናል” አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)
Next articleሚሊሻው ለአካባቢው እና ለክልሉ ሰላም መረጋጋት ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል።