
ባሕር ዳር: ግንቦት 05/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በአኹኑ ወቅት ማኅበራዊ ሚዲያ ዋነኛ የመረጃ መለዋወጫ መድረክ ነው። ይኹን እንጂ በተለይ ከጤና ጋር የተያያዙ መረጃዎች ሲተላለፉ የሚታዩ ክፍተቶች እና ሊከተሉ የሚችሉ የጤና አደጋዎች አሳሳቢ ናቸው።
የኅብረተሰብ ጤና ሳይንስ ስፔሻሊስቱ ዶክተር መኮንን አይችሉህም
በማኅበራዊ ሚዲያ የሚተላለፉ መረጃዎች ጥራት፣ የባለሙያዎች ሥነ ምግባር እና የኅብረተሰቡ ጥንቃቄ ሊታዩ የሚገባቸው ወሳኝ ነጥቦች እንደኾኑ ያነሳሉ።
#ኅብረተሰቡ በማኅበራዊ ሚዲያ የሚያገኛቸውን የጤና መረጃዎች ሳያረጋግጥ ከመቀበል ይልቅ የመረጃውን ትክክለኛነት ማወቅ እና ፈቃድ ካላቸው የሕክምና ባለሙያዎች ወይም ተቋማት ማረጋገጥ ለጤና ዋስትና ነው።
#ሰዎች በማኅበራዊ ሚዲያ የሚያዩትን ነገር ሁሉ በራሳቸው ላይ ከመሞከራቸው በፊት
የመረጃውን ምንጭ እና የመረጃ ሰጭውን ማንነት መመርመር እና በአካል ወደ ሕክምና ተቋም በመሄድ ማረጋገጥ እንደሚገባቸውም መክረዋል።
#በማኅበራዊ ሚዲያ የሚተላለፉ የጤና መረጃዎች እና ማስታወቂያዎችም ሙያዊ መርሕን የተከተሉ እንዲኾኑ ጥብቅ ቁጥጥር መደረግ አለበት ባይ ናቸው።
መረጃዎችን በጥንቃቄ መመርመር፣ ባለሙያዎች ሥነ ምግባርን መጠበቅ እና መንግሥት የቁጥጥር ሥራውን ማጠናከር የጤና ቀውስን ለመከላከል ወሳኝ መፍትሄዎች መኾናቸውን ነው ዶክተር መኮንን ያነሱት።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
See less
