ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለስምንት ምሁራኑ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ።

13

 

ባሕር ዳር: ግንቦት 04/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለስምንት ምሁራኑ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል።

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ ግንቦት 3/2018 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ሥብሠባ፤ በምርምር፣ በመማር ማስተማር እና በከፍተኛ የማኅበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ ላቅ ያለ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ስምንት ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ እድገት መስጠቱን አስታውቋል።

ምሁራኑ ለዓመታት በዕውቀት ሽግግር እና በሳይንሳዊ ምርምር ዘርፍ ላሳዩት ትጋትና ለሀገራዊ ዕድገት ላበረከቱት የማይተካ ሚና ይህ ከፍተኛ የአካዳሚክ ማዕረግ የሚገባቸው መኾኑ በቦርዱ ተረጋግጧል ነው የተባለው።

የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ያገኙ ምሁራን:-

1. ፕሮፌሰር ዓባይነህ ሙንሼ አብተው – በባዮሜዲካል ሳይንስ (Biomedical Sciences)

2. ፕሮፌሰር አያሌው ወንዴ መለሰ – በውኃ አካላት ኢኮሎጂ እና አሥተዳደር (Wetland (Aquatic) Ecology and Management)

3. ፕሮፌሰር ዳዊት አስራት ጌታሁን – በ (Educational Psychology)

4. ፕሮፌሰር ደሳለኝ እጅጉ ብርሐኔ – በዱር እንስሳት ኢኮሎጂ እና ጥበቃ (Wildlife Ecology & Conservation)

5. ፕሮፌሰር ፍቅረሰላም ጋረድ መንግሥቱ –በኮሙኒኬሽን ኢንጂነሪንግ (Communication Engineering)

6. ፕሮፌሰር ጌታሁን የማታ ሉሌ – በዕፅዋት ኢኮፊዚዮሎጂ (Plant Ecophysiology)

7. ፕሮፌሰር ጌትነት ታምሩ ጥግነህ– በ Inorganic Chemistry

8. ፕሮፌሰር ማተብ ታፈረ ገድፈው – በትምህርት ፖሊሲ እና አመራር (Education Policy and Leadership)

ከባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ወደፊትም በምርምር እና በፈጠራ ሥራዎቻቸው የዓባይ ጓዳ የኾነችውን እናት ዩኒቨርሲቲያቸውን እና ሀገራቸውን እንዲያገለግሉ አሳስበዋል።

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous articleፓርቲዎች ሕግን እና ሀገርን አስቀድሞ መንቀሳቀስ መርሐቸው ሊኾን ይገባል።
Next articleሀሰተኛ መረጃን መከላከል ለዴሞክራሲያዊ የምርጫ ሂደት ወሳኝ ነው።