
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 02/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የምዕራብ ጎጃም ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ከጃቢ ጠህናን ወረዳ እና ፍኖተሰላም ከተማ ጋር በጋራ በመኾን ለ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ የምርጫ ቅስቀሳ፣ የምልክት ማስተዋወቅ እና የድጋፍ ሰልፍ በፍኖተሰላም እየተካሄደ ነው።
በመርሐ ግብሩ የዞን፣ የፍኖተሰላም ከተማ እና የጃቢ ጠህናን ወረዳ መሪዎች እና የፓርቲው አባላት እና ደጋፊዎች ተሳትፈዋል። ”ኢትዮጵያ ወደ ተምሳሌት ሀገር” በሚል መሪ መልእክ ነው መርሐ ግብሩ የተካሄደው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
