
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 27/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በመድረኩ ላይ የክልል ምክር ቤት አማካሪ ወይዘሮ ሰብለ አስማማው የብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወይዘሮ ሀብታም አውደው እና የቀጠናው ኮር አዛዥ ብርጋዴየር ጀኔራል አዲሱ ማህመድ ተገኝተዋል።
ውይይቱ በዋናነት ያተኮረው በአካባቢው አስተማማኝ ሰላም ማስፈን በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ያተኮረ ነው። የፅንፈኛ ቡድኑን የጥፋት ተልዕኮ የከተማዉ አመራሮችና ኅብረተሰቡ በመረዳት ከሠራዊቱና ከክልሉ የፀጥታ ኀይል ጋራ ወደፊት በጋራ በሚሠሩ ሥራዎች ላይ የጋራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
የክልሉ ምክር ቤት አማካሪ ወይዘሮ ሰብለ አስማማው የከተማው መሥተዳድር ከመከላከያ ሠራዊት ጋር በመሆን የሕዝቡን ሰላም ለማረጋገጥና የልማት ሥራዎች ያለምንም ስጋት እንዲከናወኑ በትኩረት እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል።
የቀጠናዉ ኮር አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል አዲሱ ማህመድ ፣ ሠራዊቱ የሕዝብን ደኅንነት የመጠበቅ ግዳጁን በብቃት እየተወጣ የመጣ ፣ ከሕዝብና ከአመራሩ ጋር ያለውን ግንኙነት ይበልጥ የሚያጠናክር አስተማማኝ ቁመና ላይ እንዳለ ገልፀዋል። መድረኩ በአካባቢው የተጀመሩ የሰላም ጥረቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ እንደሚያግዝ ተናግረዋል።
የሕዝብ ተሳትፎ ሰላምን በዘላቂነት ለማረጋገጥ ወሳኝ በመሆኑ ማንኛውንም የፀረ-ሰላም ኃይሎችን እንቅስቃሴ ነቅቶ በመከታተል ለጸጥታ አካላት ጥቆማ መስጠት እንደሚገባ አጽንኦት ተሰጥቶበታ። መረጃው የምሥራቅ እዝ ነው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
