ሕገ ወጥ ግብይትን በመከላከል ማኅበረሰቡን ከብዝበዛ መታደግ ይገባል።

11
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 27/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል የምርት እና ግብይት፣ የገበያ አረጋጊ፣ የሕገ ወጥ እና ፀረ ኮንትሮባንድ ጥምር ግብረ ኃይል የወንጀል ጉዳዮች ቴክኒክ ኮሚቴ የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸሙን እየገመገመ ይገኛል።
የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ኀላፊ ብርሃኑ ጎሽም በንግድ ሥርዓቱ የሚፈጸሙ ሕገ ወጥ ድርጊቶችን ለመከላከል አሥተዳደራዊ እርምጃዎችን በመውሰድ ማኅበረሰቡን ካለአግባብ ወጭዎች ለመታደግ ጥረት ሲደረግ መቆየቱን ገልጸዋል።
“ሕገ ወጥ ግብይት እና ምርትን መደበቅ ማኅበረሰቡን ለብዝበዛ እየዳረገ ነው” ብለዋል። ማኅበራዊ ቀውስን የሚያመጣ ተግባር ነውም ብለዋል።
ሕገ ወጥ ንግድን እና ኮንትሮባንድን ለመከላከል በቅንጀት እየተሠራ መኾኑንም ነው ያነሱት። በተለይም ባለፉት ዘጠኝ ወራት ሕገ ወጥ ኬላዎችን የመከላከል ተግባራት በትኩረት ተሠርቷል ብለዋል።
በሕግ ማስከበር ተግባር እና በተለያዩ የግብይት ሥርዓቶች ቁጥጥር የማድረግ እና ሀብት የማስመለስ ሥራም ተሠርተል ነው ያሉት።
በተሠራው የሕገ ወጥ ንግድ ቁጥጥር ተግባርም ከ58 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ነዳጅ መያዙን ጠቁመዋል። ያም ኾኖ በሚፈለገው ልክ ለውጥ አንዳልመጣ እና ግብረ ኃይሉ ወቅቱን የዋጀ ሕገ ወጥ ተግባራትን የመከላከል ኀላፊት እንዳለበትም ገልጸዋል።
ሕጋዊ የንግድ ሥርዓት አንዲዘረጋ መሥራት እንደሚገባም በአጽንኦት ገልጸዋል።
ዘጋቢ፦ ሥራውድንቅ ደሳለው
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleወጣቱ የአባቶቹን የጀግንነት ሥነ-ልቦና ተላብሶ ለሰላም ዘብ ሊቆም ይገባል።
Next articleአባቶች ለነጻነት ወደቁ፤ እኛ ለታላቅነት እንቆማለን።