ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የኢትዮጵያን የአምራች ዘርፍ ለማስፋፋት የሚደረገውን ጥረት የሚያጠናክረውን አራተኛውን ‘ኢትዮጵያ ታምርት’ ኤክስፖ 2018 ዛሬ በይፋ መርቀው ከፍተዋል።

32


‎ኤክስፖው እስካሁን ያሳያቸው እና የተመዘገቡ ዋና ዋና ስኬቶች፦

👉የአምራች ዘርፉ ግብዓት አቅርቦት በዓመት ከ9 ሚሊዮን ወደ 15 ሚሊዮን ቶን አድጓል፤

👉ለአዳዲስ የኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንቶች ከ3 ነጥብ 4 ጊጋ ዋት በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል ቀርቧል፤

‎👉ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የሚቀርበው የፋይናንስ አቅርቦት ከ8 ነጥብ 1 ቢሊዮን ወደ 50 ቢሊዮን ብር ያደገ ሲሆን ለከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች ደግሞ ከ262 ቢሊዮን ብር በላይ ከፍ ብሏል፤

👉ለዘርፉ ከ2 ነጥብ 28 ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ተመድቧል፤

👉የፋብሪካዎች የማምረት አቅም ከ47 በመቶ ወደ 67 በመቶ አድጓል፤

‎👉የማምረት አቅምና ዕድገት ከ4 ነጥብ 8 በመቶ ወደ 10 ነጥብ 7 በመቶ ከፍ ያለ ሲሆን፣ በቀጣይም ተጨማሪ ዕድገት ይጠበቃል፤

👉ምርትን በሀገር ውስጥ በመተካት እስከ 4 ነጥብ 85 ቢሊዮን ዶላር ማዳን የተቻለ ሲሆን የወጪ ንግድም ከፍተኛ እድገት እያሳየ ይገኛል፤

‎👉ከ2 ሺህ 800 በላይ ኢንቨስትመንቶችን መሳብ የተቻለ ሲሆን፣ ለ1 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዜጎች የሥራ ዕድል ተፈጥሯል።

‎ኤክስፖው ኢንዱስትሪዎችን የሚያስተሳስር፣ ኢንቨስትመንትን የሚስብ፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ አምራቾችንና በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ጎብኝዎችን የሚያገናኝ ቁልፍ ሀገራዊ መድረክ ሆኗል።

‎በአጠቃላይ የኤክስፖው መከፈት የአምራች ዘርፉ ለኢኮኖሚ ዕድገት፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራና ለዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ያለውን ፋይዳ በማጉላት የኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ ሽግግር እያፋጠነ መሆኑን ያሳያል።

#PMOEthiopia

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ለሚመጣው ትውልድ ጽኑ፣ በኢንዱስትሪ የበለጸገች እና ራሷን የቻለች ኢትዮጵያን እንገነባለን” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)
Next article“ሀገር እና ሕዝብን የሚያስከብሩ፣ ለትውልድም የሚተርፉ ሥራዎች እየሠራን እንገኛለን” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ