ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) “ጎበዝ ሶላር ሴል” ማምረቻን ጎበኙ።

15

 

ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በማኅበራዊ ገጻቸው ባጋሩት መልእክት ዛሬ ጠዋት በአዲስ አበባ በሁዋጂያን ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ውስጥ የሚገኘውን “ጎበዝ ሶላር ሴል” ማምረቻን መጎብኘታቸውን ገልጸዋል።

‎ይህ ፋብሪካ በ2025 ኢትዮጵያ ውስጥ ኢንቨስት ያድርጉ ፎረም (Invest in Ethiopia Forum) አማካኝነት በተፈረመው ስምምነት መነሻ በ100 ሚሊየን ዶላር የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ የተቋቋመ ነው።

‎በውጤታማ ድጋፍ እና ክትትል በስድስት ወራት ብቻ እውን የሆነው “ጎበዝ ሶላር ሴል” ማምረቻ ዘመናዊ ማሽኖች እና በቴክኖሎጂ የተዋቀረ ነው። በ38 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈው ማምረቻው ለበርካታ ዜጎች የስራ እድልም ፈጥሯል።

‎በመጀመሪያ ምዕራፍ 2 ጌጋዋት ዓመታዊ የማምረት አቅም ያለው ፋብሪካው የኢትዮጵያን የኃይል ፍላጎት ሙሉ በሙሉ ከታዳሽ ኃይል ለማድረግ ለተጀመረው ሀገራዊ ርዕይ እውን ለማድረግ ተደማሪ አቅም ፈጥሯል።

‎በተጨማሪም በኢንደስትሪ ፓርኩ ውስጥ የሚገኘውን የጫማ ማምረቻ እና ንዑስ የኤሌክትሪክ ጣቢያን ተመልክቻለው ነው ያሉት።

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ( ዶ.ር) በመጋቢት እና ሚያዝያ 2018 ዓ.ም ያከናዎኗቸው ተግባራት
Next article🪪 የዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) የካርድ ኅትመት ጠይቀው ወዲያው መረከብ ተቻለ!!