የአፈር ማዳበሪያ እና ምርጥ ዘር እያሰራጨ መኾኑን ሰሜን ጎጄም ዞን አስታወቀ።

5

 

ባሕርዳር፡ ሚያዝያ 23/2018ዐዓ.ም (አሚኮ) የሰሜን ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ የ2018/19 የሰብል ልማት የንቅናቄ መድረክ እያካሄደ ነው።

የሰሜን ጎጃም ዞን ምክትል አሥተዳዳሪ እና የግብርና መምሪያ ኀላፊ በለጠ ጥጋቡ ዞኑ በ2017/2018 የምርት ዘመን ከ321ሺህ 500 በላይ ሄክታር መሬት በሁሉም የሰብል ዓይነቶች በመዝራት ከ15 ሚሊዮን 433ሺህ በላይ ኩንታል ምርት ማምረት መቻሉን አስታውሰዋል።

ምርታማነቱንም በሄክታር ማሳደግ መቻሉን ጠቅሰዋል። ለዚህም ወደ 32ሺህ ሄክታር ጭማሪ መሬት ታርሷል ነው ያሉት።

በተያዘው 2018/2019 የምርት ዘመን ደግሞ ካለው 321ሺህ 500 በላይ መሬት 10ሺህ 500 ሄክታር በመጨመር 332ሺህ ሄክታር መሬት ለማረስ ታቅዶ እየተሠራ ነው ብለዋል። በዚህም 17 ሚሊዮን 926ሺህ በላይ ኩንታል ምርት ለማግኘት ታቅዶ እየተሠራ እንደኾነም ጠቅሰዋል።

ለዚህም እንደ ዞን 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ኩንታል ዳፕ እና ዩሪያ ማዳበሪያ እንደሚያስፈልግም ገልጸዋል። ከዚህም መካከል አሁን ላይ 50 በመቶ የሚኾነው ወደ ዞኑ መካዝን ገብቶ በኅብረት ሥራ ማኅበራት አማካኝነት እየተሠራጨ መኾኑን ተናግረዋል።

ለምርት ዘመኑ ከ32ሺህ ኩንታል በላይ የበቆሎ ምርጥ ዘር ያስፈልጋል። አሁን ላይ በሁሉም ወረዳዎች ከ40ሺህ በላይ ኩንታል የበቆሎ ምርጥ ዘር ቀርቦ እየተሠራጨ ነው ብለዋል።

ዘጋቢ፦ ሮዛ የሻነህ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous articleየሠራተኞችን መብት እና ደኅንነት ለማስጠበቅ እየተሠራ ነው።
Next articleባሕር ዳር ከተማ በለውጥ ውስጥ ትገኛለች።