6

የበደልነውን ሕዝብ ለመካስ ዝግጁ ነን።

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 21/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በደቡብ ጎንደር ዞን ታች ጋይንት ወረዳ እና አካባቢው በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀብለዋል።
የሰላም አማራጭ የተቀበሉትን ታጣቂዎች በአካባቢው የሚንቀሳቀሰው የሀገር መከለካያ ሠራዊት መሪዎች እና የወረዳው የሥራ ኀላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የሰላም አማራጭን ተቀብለው የገቡት ታጣቂዎች በትጥቅ ትግል የትኛውንም ጥያቄ መመለስ እንደማይቻል ተናግረዋል።

‎ሌሎች በጫካ ያሉ ወንድሞቻችን የሰላም አማራጭን በመጠቀም ከትጥቅ ትግል ይልቅ ሰላምን በመምረጥ በልማት ሊሳተፉ ይገባል ነው ያሉት።

‎ከታች ጋይንት ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው በማወቅም ኾነ ባለማወቅ የበደልነውን ሕዝብ ለመካስ ዝግጁ ነን ብለዋል።

‎የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous articleየአምባሳደር ያለው አባተ የቀብር ሥነ ሥርዓት በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጸመ።
Next articleየዲጅታል መረጃዎች ዘብ!