የጸጥታ ኀይሉ ያለውን ዝግጅነት እና ቅንጅት በማጠናከር የሕዝቡን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ እየሠራ ነው።

8
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 21/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በሀገር መከላከያ ሠራዊት የምሥራቅ እዝ ምክትል አዛዥ ለኦኘሬሽናል ሜጀር ጀኔራል ተስፋዬ ረጋሳ በአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ዳንግላ ወረዳ ዙሪያ በጊሳ ንዑስ ወረዳ ተሠማርቶ ከሚገኘው ከአማራ ክልል የጸጥታ ኀይል ጋር በጸጥታ እና ደኅንነት ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።
በአካባቢው አስተማማኝ ሰላምና መረጋጋት ለማስፈን ሁሉም የጸጥታ አካላት ከኅብረተሰቡ ጋር የተቀናጀ ጥምረት በመፍጠር ተናቦ መሥራት እንደሚያስፈልጋቸው ገልጸዋል።
በአካባቢው የሚንቀሳቀሰው የሀገር መከላከያ ሠራዊት የኮር አዛዥ ብርጋዲዬር ጀኔራል አዲሱ መሐመድ የጸጥታ ኀይሉ ያለውን ዝግጅነት እና ቅንጅት በማጠናከር የሕዝቡን ሰላምና ደህንነት የማረጋገጥ ሥራ እየሠራ መኾኑን ተናግረዋል። ሥራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አሥገንዝበዋል።
የውይይቱ ተሳታፊዎችም ከሀገር መከላከያ ሠራዊት ጋር በቅንጅት ተልዕኮ መፈጸማቸው ውጤታማ መኾናቸውን ተናግረዋል። ከሀገር መከለካያ ሠራዊት የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው በቀጣይም ለላቀ ውጤት ዝግጁ መኾናቸውም ጠቁመዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleከቀውስ ባሻገር መሻገር