
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 20/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በደቡብ ሱዳን በደረሰ የአውሮፕላን አደጋ አብራሪውን ጨምሮ ሁሉም ተሳፋሪዎች ሕይወታቸው ማለፉን አፍሪካ ኒውስ ዘግቧል።
የሀገሪቱ የሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን አነስተኛ አውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩት ሁሉም ተሳፋሪዎች እና አብራሪው በአደጋው መሞታቸውን አስታውቋል።
የሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን እንዳስታወቀው በስዓቱ የነበረው አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ እና ዝቅተኛ የዕይታ መጠን ለአደጋው መከሰት እንደምክንያት ገልጿል።
በጁባ የተከሰተው አሳዛኝ አደጋ በከተማዋ ዳርቻ አካባቢ የተፈጠረ ሲኾን የ14 ሰዎችን ሕይወት ቀጥፏል።
ከመንገደኞች መካከል ሁለቱ የኬኒያ ዜግነት ያላቸው ሲኾን የተቀሩት የደቡብ ሱዳን ዜግነት ያላቸው መኾኑን ዘገባው ጠቁሟል።
የሀገሪቱ ባለሥልጣናት እንዳሉት ከጁባ 20 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የአደጋ ሁኔታውን ለመገምገም የምርመራ ቡድን ተልኳል።
ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
