
ባሕር ዳር፡ ሚያዚያ 20/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል መንግሥት የቀድሞውን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ያለው አባተ ኀልፈት አስመልክቶ የሀዘን መግለጫ አውጥቷል። የመግለጫው ሙሉ ይዘት እንደሚከተለው ቀርቧል፦
የቀድሞው የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ እና በተለያዩ ከፍተኛ የመንግሥት ኀላፊነቶች ሀገራቸውን ያገለገሉት አምባሳደር ያለው አባተ ረታ ከዚህ ዓለም በሞት በመለየታቸው የተሰማንን ጥልቅ ሃዘን እየገለጽን፤ በሕይወት ዘመናቸውም የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት አፈ ጉባኤ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ፣ በአማራ ክልል የሥራና ከተማ ልማት ቢሮ ኃላፊ፣ የወጣቶች፣ ስፖርትና ባሕል ቢሮ ኀላፊ እንዲሁም በብራዚል የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር በመሆን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ኀላፊነታቸውን ተወጥተዋል፡፡
አምባሳደር ያለው አባተ ባደረባቸው ሕመም ምክንያት የሕክምና እርዳታ ሲደረግላቸው ከቆዩ በኋላ ሚያዝያ 19/2018 ዓ.ም ሕይወታቸው በማለፉ ለቤተሰብ፣ ለዘመድ አዝማድ እና ለወዳጅ ወገኖች ከልብ መጽናናትን እንመኛለን፡፡
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት
ሚያዝያ 2ዐ/2ዐ18 ዓ.ም
ባሕር ዳር
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
