
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 14/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቴክስታይል እና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩትን ጎብኝተዋል።
አምባሳደሩ ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት መንገሻ አየነ (ዶ.ር) እና ከሌሎች የዩኒቨርሲቲው መሪዎች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።
በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቴክስታይል እና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በፋሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ በርካታ ሥራዎችን እያከናወነ ነው። በተግባር የተደገፈ ትምህርት በመስጠት በኢትዮጵያ ውስጥ የራሱን አሻራ እያሳረፈም ይገኛል።
የሀገር ውስጥ ምርቶችን በዘመናዊ መልኩ የሚሠራው ኢንስቲትዩቱ በፋሽን ቴክኖሎጂ እያሳየ የሚገኘው ሥራ የሚደነቅ መኾኑ በዕለቱ ተገልጿል።
አንጋፋው ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ባለፉት ዓመታት በተለያዩ የትምህርት መስኮች ለኢትዮጵያ እና ለተቀረው ዓለም በርካታ ምሁራንን አበርክቷል። እያበረከተም ይገኛል።
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ራሱን እያሳደገ እና ዘመኑን እየዋጀ የመጣ ታላቅ ተቋም ነው።
ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
