
ባሕር ዳር፡ ሚያዚያ 13/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የምሥራቅ እዝ አንድ ኮር አባላት ባለቤቷ በጽንፈኛ ኃይሎች በግፍ ለተገደለባት ግለሠብ የ300 ሺ ብር የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል።
ወይዘሮ የሺእመቤት ከቤ የተባለችው ግለሰብ በሰሜን ጎጃም ዞን መራዊ ከተማ ነዋሪ ናት። በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ፅንፈኛ ኃይሎች መምህር ደረጄ አቀማመጥ ቦጋለ የተባለውን የትዳር አጋሯን መጋቢት 11/07/2017 ዓ.ም በግፍ ገድለውባታል።
የ4 ልጆች እናት መኾኗን እና እነዚህን ልጆች ያለ አባት የማሣደግ ኀላፊነት እንደተጣለባት በመገንዘብ ነው የምሥራቅ ዕዝ አባላት ድጋፉን ያደረጉላት።
በአካባቢው ግዳጃቸውን በመፈፀም የሚገኙት የምሥራቅ ዕዝ አንድ ኮር ሠራዊት አባላት ከደምወዛቸው በማዋጣት ነው የ300 ሺህ ሺህ ብር የደገፉ።
ገንዘቡን ያስረከቡት የሠራዊቱ ከፍተኛ አመራር ብርጋዴር ጄኔራል አዲሱ መሐመድ እንደተናገሩት ሠራዊቱ ይህን የገንዘብ ድጋፍ ያደረገው ከራስ በፊት ለሕዝብ እና ለሀገር በሚለው እሴቱ እና ይህንን እሴቱን በተግባር የማዋል ልምዱን በማስቀጠል ነው ብለዋል። ይህ ጠንካራ የሠራዊቱ እሴት ቀጣይ እንደሚኾንም ተናግረዋል።
ሠራዊቱ ከሕዝብ የወጣና ለሕዝብ ሰላም ሲል ያለውን ሁሉ የሚሰጥ መሆኑንም አረጋግጠዋል።
ወገን እንዳይቸገር ሠራዊቱ ከሚመገበውም ላይ ጭምር እየቀነሰ በማካፈል ከሕዝብ ጎን የሚቆም እሴት ያለው በመሆኑ ወደፊትም አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። መረጃው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ምሥራቅ ዕዝ ነው።
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
