
ደብረታቦር: ሚያዚያ 12/2018 (አሚኮ) በደቡብ ጎንደር ዞን የፋርጣ ወረዳ ነዋሪዎች ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምጽ ለመስጠት የሚያስችላቸውን የመራጭነት ካርድ እየወሰዱ ነው።
ነዋሪዎቹ ልማትን የሚያፋጥን እና ኢትዮጵያን ካደጉት ሀገራት ተርታ የሚያሰልፍ ፓርቲ ለመምረጥ የምርጫ ካርድ መውሰድ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር መኾኑን ገልጸዋል።
ከአሚኮ ጋር ቆይታ ያደረጉት ነዋሪዎቹ የዜጎች ዴሞክራሲያዊ መብት በሚረጋገጥበት ምርጫ ለመሳተፍ ኅብረተሰቡ በዝግጅት ላይ መኾኑን ተናግረዋል።
የሚያስተዳድራቸውን እና የልማት ጥያቄዎቻቸውን የሚመልስላቸውን ፓርቲ በመምረጥ መብታቸውን እንደሚጠቀሙም ገልጸዋል።
የምዝገባው ቀን መራዘሙም በተለያዩ ምክንያቶች ካርድ ያልወሰዱ ዜጎች ዕድሉን እንዲያገኙ ማድረጉን ጠቁመዋል። የሚመራቸውን አካል ለመምረጥ የምርጫ ቀናትን በጉጉት እየጠበቁ መኾናቸውን ጠቁመዋል።
እስካሁን ካርድ ያልወሰዱ የኅብረተሰብ ክፍሎች እንዲመዘገቡ ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል።
የያዙትን ካርድ ድምጽ እስከሚሰጡበት ዕለት ድረስ በጥንቃቄ መያዝ እንደሚያስፈልግ አመላክተዋል።
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
