
ፍኖተሰላም: ሚያዚያ 12/2018 (አሚኮ) ለቀጣይ አምስት ዓመታት የሚመራቸውን ለመምረጥ ካርድ አውጥተው በመጠባበቅ ላይ መኾናቸውን በምዕራብ ጎጃም ዞን የፍኖተ ሰላም ከተማ ነዋሪዎች ተናግረዋል።
አሚኮ ያነጋገራቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ምርጫ ለሀገረ መንግሥት ግንባታ ወሳኝ እና የሥልጡንነት ምልክት ነው ብለዋል። ለዚህ ደግሞ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ለቀጣይ አምስት ዓመታት ሊመራ የሚችለውን መንግሥት በካርድ መምረጥ እንደሚያስፈልግ አንስተዋል።
ነዋሪዎቹ ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ካርድ በማውጣት በምርጫው ለመሳተፍ ዝግጁ ኾነው እየተጠባበቁ እንደሚገኙም ነው የጠቆሙት።
ምርጫ ማካሄድ አሁን ላይ ያሉ የጸጥታ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ሚናው የጎላ መኾኑንም ገልጸዋል።
በተለይም ምርጫው በስኬት እንዲጠናቀቅ ሰላም አስፈላጊ መኾኑን የተናገሩት ነዋሪዎቹ ሁሉም ለሰላም መሥራት እንደሚጠበቅበት ተናግረዋል።
በቀጣይ ቀሪ ቀናት ማኅበረሰቡ ካርድ በማውጣት የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርግ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
