
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 09/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥን ብትከፍትም ከአሜሪካ ጋር ስምምነት ላይ እስከምትደርስ ድረስ ወደ ወደቦቿ የሚደረጉ ጉዞዎች ላይ የተጣለው እግድ “በሙሉ ኃይል እና ተፈጻሚነት” እንደሚቀጥል ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስታውቀዋል።
ፕሬዝዳንቱ በትሩዝ የማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት
ኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥን ክፍት በማድረጓ አመስግነዋል።
ሁለተኛው ዙር የአሜሪካ እና ኢራን የሰላም ድርድር በዚህ ሳምንት መጨረሻ ሊካሄድ እንደሚችል ገልጸዋል፡፡
የሆርሙዝ ሰርጥ አሁን ለንግድና ጉዞ ክፍት መሆኑን ገልጸው፣ ከኢራን ጋር የሚደረጉ ንግግሮች በፍጥነት ሊጠናቀቁ መቃረባቸውን አስታውቀዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
