“ሀገርን የማሻገር ሥራችን ተጠናክሮ ይቀጥላል” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ

4

 

ባሕር ዳር፡ ሚያዚያ 07/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒሰትር ተመስገን ጥሩነህ እና ሌሎችም ከፍተኛ መሪዎች በደቡብ ወሎ ዞን ተሁለደሬ ወረዳ አሎማ ክላስተር በበጋ መስኖ የለማውን የደረሰ የስንዴ ማሳ ተመልክተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባጋሩት መልእክት የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ሀገራችን በምግብ ራሷን ለመቻል የጀመረችው ጉዞ በተግባር ስር እየሰደደ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል።

የመደመር መንግሥት ለበጋ መስኖና ለስንዴ ምርታማነት የሰጠው ትኩረት የዜጎችን ሕይወት እየቀየረና የሀገርን የምግብ ሉዓላዊነት እያረጋገጠ እንደሚገኝም አመላክተዋል። “ዛሬ የተመለከትነው የስንዴ ልማት የራዕያችንን ውጤት፣ የሀሳባችን መሬት መንካትና ፍሬ የማግኘታችን ተጨባጭ ማሳያ ነው” ሲሉ ገልጸዋል።

አርሶ አደሮችን በተደመረ አቅም በማትጋት እና የተፈጥሮ ፀጋዎቻችንን በመጠቀም በሁሉም መስክ ሀገርን የማሻገር ሥራችን ተጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየመንግሥት ሠራተኞችን መረጃ የማረጋገጥ ሥራ ሊተገበር ነው።