ብሩኖ ፈርናንዴዝ በዳኞች እና በቫር ውሳኔዎች ላይ ቅሬታውን ገለጸ።

0
56

የማንቸስተር ዩናይትድ አምበል ብሩኖ ፈርናንዴዝ ከማንቸስተር ዩናይትድ እና ከሊቨርፑል ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ ለኢኤስፒኤን ብራዚል በሰጠው መግለጫ፣ በዳኞች አወሳሰን እና በቫር (ቪዲዮ ረዳት ዳኛ) አሠራር ላይ ያለውን ከፍተኛ ብስጭት ተናግሯል።

ፈርናንዴዝ በንግግሩ ቅሬታ እያቀረበ እንዳልኾነ ቢገልጽም፣ ዳኞች በውድድር ዘመኑ መጀመሪያ ላይ ራሳቸው ያብራሩትን ሕግ በሜዳ ላይ በትክክል እንደማያውቁት ተችቷል።

አያይዞም “ሕጎቹን እንዲያብራሩልን ከዳኞች ጋር እጅግ በጣም ብዙ ሥብሠባዎችን እናደርጋለን፤ ነገር ግን መጨረሻ ላይ ዳኞቹ ራሳቸው ሕጎቹን አያውቋቸውም” ሲል ገልጿል።

በጨዋታው ላይ አራት የሜዳ ዳኞች እንዲሁም ሌሎች ሁለት ዳኞች በቫር ክፍል ውስጥ እንደሚገኙ ያስታወሰው ፖርቱጋላዊው አማካይ፣ በሜዳ ላይ ያሉት ውሳኔዎችን መወሰን ከባድ ሊኾን እንደሚችል ቢረዳም፣ የቫር ዳኞች ምስሉን ደጋግመው በዝግታ የማየት ዕድል እያላቸው ስህተት መሥራታቸውን አጥብቆ ተቃውሟል።

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ኅዳር_15_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here