ሊቨርፑል በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ታሪክ 700 ድሎችን ያስመዘገበ ሦሥተኛው ክለብ ኾነ።

0
85

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ታሪክ 700ኛ ድሉን በማስመዝገብ ይህንን ታሪካዊ ሪከርድ የተቀላቀለ ሦሥተኛው ክለብ መኾን ችሏል።

በውድድሩ ታሪክ ከሊቨርፑል በፊት ይህንን የድል ቁጥር ማሳካት የቻሉት ሁለት ክለቦች ብቻ ሲኾኑ፣ እነሱም 776 ድሎችን በማስመዝገብ ቀዳሚ የኾነው ማንቸስተር ዩናይትድ እና 728 ድሎች ያሉት አርሰናል ናቸው።

ሊቨርፑል በሊጉ ያለውን ረጅም ታሪክ እና የበላይነት በዚህ አዲስ የ700 ድል ስኬት አጠናክሮ ቀጥሏል።

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ኅዳር_15_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here