በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ 4ኛ ዙር የምድብ ጨዋታ በባ/ዳር አለም አቀፍ ስታዲየም ከሞዛምቢክ ጋር የተጫወተው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን 1 ለ 0 ተሸንፏል።
በጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ ክፍለ ጊዜ 38ኛው ደቂቃ ላይ የዋልያዎቹ ተከላካዮች የሰሩትን ስህተትና መዘናጋት ተጠቅሞ 13 ቁጥሩ ራቲፎ የሞዛምቢክን ብቸኛና የማሸነፊያ ግብ አስቆጥሯል።
ከረፍት መልስ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የተሻለ ብልጫ ወስዶ ተንቀሳቅሷል።
ኾኖም ቢኒያም ፍቅሩ፣ቸርነት ጉግሳና አንተነህ ተፈራ ያገኟቸውን የግብ እድሎች ሳይጠቀሙባቸው ቀርተዋል።ጠቅላላ ጨዋታውም በሞዛምቢክ 1 ለ 0 አሸናፊነት ተጠናቋል።
ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጰያ ከሱዳን ጋር እኩል 3 ነጥብ ብቻ በመያዝ ለአፍሪካ ዋንጫ የማለፍ እድሏ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል።
ምድቡን ሴኔጋል በ10 ነጥብ ስትመራ ሞዛምቢክ በ7 ነጥብ ትከተላለች።
#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ኅዳር_08_2019_ዓ_ም
በኃይሌ አበራ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



