‎ለ2027 የአፍሪካ ዋንጫ የትኞቹ ሀገራት ቀድመው ማለፋቸውን አረጋገጡ?

0
36

‎የአፍሪካ ዋንጫ 4ኛ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታዎች ሲጠናቀቁ ስድስት ሀገራት ኬኒያ፣ ታንዛኒያ እና ዩጋንዳ በጥምረት ለሚያዘጋጁት ውድድር ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።

‎‎ከምድብ አንድ ሰሜን አፍሪካዊቷ ሀገር ሞሮኮ ያደረገቻቸውን አራት ጨዋታዎች በሙሉ በማሸነፍ በ12 ነጥብ የአፍሪካ ዋንጫ ትኬቷን ቆርጣለች።

‎‎ሞሮኮ በአራተኛ የምድብ ጨዋታ ትናንት ኒጀርን ከሜዳዋ ውጭ 1 ለ 0 ካሸነፈች በኋላ ለ2027ቱ የአፍሪካ ዋንጫ ማለፏን አረጋግጣለች።

‎‎ሞሮኮ በ12 ነጥብ ማለፏን ባረጋገጠችበት ምድብ አንድ ጋቦን በስድስት ነጥብ ሁለተኛ፣ ኒጀር እና ሌሴቶ ደግሞ በሦሥት ነጥብ ሦሥተኛ እና አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

‎‎የመጨረሻ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታዎች በመጋቢት ወር ሲካሄዱ ሦሥቱ ሀገራት ሞሮኮን ተከትሎ ለማለፍ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።

‎‎በምድብ ስድስት ቡርኪናፋሶ ትናንት ሞሪታኒያን በሜዳዋ 3 ለ 1 ከረታች በኋላ ለ2027ቱ የአፍሪካ ዋንጫ ማለፏን ያረጋገጠች ሌላኛዋ ሀገር ነች።

‎ከትናንቱ ድል በኋላ ነጥቧን 10 ያደረሰችው ቡርኪናፋሶ ለቀጣዩ የአፍሪካ ዋንጫ ማለፏን አረጋግጣለች።

‎‎ከዚሁ ምድብ ስድሰት ባሳለፍነው ሰኞ ማዕከላዊ አፍሪካን 1 ለ 0 ያሸነፈችው ቤኒን በእኩል 10 ነጥብ የአፍሪካ ዋንጫ ማለፏን ስታረጋግጥ ሞሪታንያ ሦሥት መካከለኛው አፍሪካ ደግሞ ያለምንም ነጥብ ከምድቡ ወድቀዋል። የዚህ ምድብ ቀጣይ ሁለት ጨዋታዎችም ለመርሐ ግብር ሟሟያ ብቻ የሚደረጉ ይኾናል።

‎‎‎በምድብ ሰባት ትናንት በተደረገ ጨዋታ ኮሞሮስ ኮንጎን ከሜዳዋ ውጭ 2 ለ 0 ያሸነፈች ሲኾን ይህም ካሜሮን ሀሉት ጨዋታ እየቀራት ለአፍሪካ ዋንጫው እንድታልፍ አድርጓታል።

‎‎ኮሞሮስ ከትናንት ድሏ በኋላ ነጥቧን ሰባት በማድረስ ለአፍሪካ ዋንጫ የማለፍ ዕድሏን ስታሰፋ የኮሞሮስ ውጤት ሰኞ እለት ናሚቢያን 3 ለ 0 ያሸነፈችውን ካሜሩን በ10 ነጥብ ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፏን እንድታረጋግጥ አድርጓል።

‎‎ምድብ 11 ትናንት ሩዋንዳን 2 ለ 0 ያሸነፈችው ማሊ በ10 ነጥብ ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፏን አረጋግጣለች። ‎በዚሁ ምድበረ ላይቤሪያ ትናንት ኬፕ ቨርዴን 2 ለ 0 በማሸነፍ በማጣሪያው የመጀመሪያ ድሏን አስመዝግባለች።

‎‎ማሊ ማለፏን ባረጋገጠችበት ምድብ 11 ሩዋንዳ በስድስት ነጥብ 2ኛ ደረጃ ላይ ስትቀመጥ ኬፕ ቬርዴ እና ላይቤሪያ እኩል ሦሥት ነጥብ አላቸው።

‎‎በምድብ 10 ሞዛምቢክ ትናንት ባሕር ዳር ላይ ኢትዮጵያን 1 ለ 0 ካሸነፈች በኋላ ሰኞ ለት ሱዳንን 4 ለ 2 ያሸነፈችው ሴኔጋል በ10 ነጥብ ለአፍሪካ ዋንጫው እንድታልፍ አድርጓል።

‎‎ሴኔጋል ማለፏን ባረጋገጠችበት ምድብ 10 ሞዛምቢክ በሰባት ነጥብ 2ኛ፣ ኢትዮጵያ እና ሱዳን ደግሞ በእኩል ሦሥት ነጥብ 3ኛ እና 4ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

‎‎ባጠቃላይ ከ4ኛ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታዎች በኋላ ስድስት ሀገራት ሞሮኮ፣ ቤኒን፣ ቡርኪናፋሶ፣ ካሜሩን፣ ሴኔጋል እና ማሊ ለ2027ቱ የአፍሪካ ዋንጫ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።

‎ኬንያ፣ ታንዛኒያ እና ኡጋንዳ አዘጋጅ በመኾናቸው በቀጥታ የውድድሩ ተካፋይ ይኾናሉ።

‎#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ኅዳር_09_2019_ዓ_ም

በባዘዘው መኮንን

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here