የምዕራብ ጎጃም ዞን ባሕል፣ ቱሪዝም እና ስፖርት መምሪያ በፍኖተሰላም ከተማ ሲያካሂድ የቆየውን 22ኛው የባሕል ስፖርት ውድድር አጠናቅቋል።
በውድድሩ ሲሳተፉ አሚኮ ያገኛቸው የቋሪት እና የቡሬ ዙሪያ ወረዳ ስፖርተኞች አንዱዓለም ጌትነት እና መልሰው ሙላቴ የባሕል ስፖርት የቀደምት ባሕሎችን እሴት ለማስቀጠል የሚያገለግል መኾኑን አስረድተዋል።
ስፖርቱ የአንዱን አካባቢ ባሕል ሌላኛው የሚጋራበት ለቀጣይ ትውልድ ተጠብቆ እንዲሻገር ከፍተኛ ሚና እንዳለውም ነው የገለጹት። ቀጣይ በሚኖሩ ውድድሮች ብርቱ ፉክክር ለማድረግ ከወዲሁ ዝግጁ እንደኾኑም ጠቁመዋል።
የምዕራብ ጎጃም ዞን ባሕል፣ ቱሪዝም እና ስፖርት መምሪያ የስፖርት ዘርፍ ቡድን መሪ ምንውየለት ገበየሁ ውድድሩ በቤት ውስጥ እና ውጭ በኾኑ በ11 የባሕል ስፖርት ዓይነቶች መካሄዱን ገልጸዋል።
የአሁኑ ትውልድ የቆዩ ባሕሎችን ተቀብሎ ለቀጣዩ ትውልድ ለማሻገር ያለመ ውድድር ነው ብለዋል።
የባሕል ስፖርቶች ይዘታቸውን ጠብቀው እንዲቀጥሉ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች እና ማዘውተሪያ ስፍራዎች ላይ ሰፊ ሥራ መሥራት እንደሚጠበቅም አስገንዝበዋል።
በሁሉም የባሕል ስፖርት ዓይነቶች አሸናፊ የኾኑ ተወዳዳሪዎች በክልል ደረጃ በሚኖረው ውድድር ተሳታፊ እንደሚኾኑም ተጠቁሟል።
#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ኅዳር_08_2019_ዓ_ም
ዘጋቢ፦ ንጉስ ስንታየሁ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



