ደሴ፣ ኅዳር 06/2019 ዓ.ም (አሚኮ ደሴ) የቀድሞ የእንግሊዝ እግር ኳስ ተጫዋች እና ታዋቂው ተንታኝ ጋሪ ሊንከር፤ ማውሪሲዮ ፖቼቲኖ በማንችስተር ዩናይትድ ያለው ቆይታ በመዋቅራዊ ችግሮች ይፈተናል ብሏል።
በመጀመሪያዎቹ ጨዋታዎች እንደ ማይክል ካሪክ ሁሉ ሊሳካለት ይችላል ብሏል። ነገር ግን በክለቡ ስር የሰደዱ ችግሮች የተነሳ ከ18 ወር በኋላ በሥራ ላይ ከቆየ በእርግጠኝነት እገረማለሁ ብሏል ጋሪ ሊንከር።
ማይክል ካሪክን በመተካት የሁለት ዓመት ተኩል ውል የፈረመው ፖቼቲኖ፤ ቀያይ ሠይጣናቱ በሊጉ በ18ኛ ደረጃ ላይ በሚገኙበት እና ላለፉት 8 ጨዋታዎች ድል ባላገኙበት አስቸጋሪ ሰዓት ላይ ነው ክለቡን የተረከበው።
“አንድ ክለብ የውጤት ቀውስ ሲገጥመው ሁልጊዜም ተጠያቂ የሚደረገው አሰልጣኙ ነው ፤ የዩናይትድ ችግሮች መነሻ ከክለቡ አመራሩሮች ነው” ብሏል ተንታኙ።
“ባለፉት 10 ዓመታት የነበሯቸውን አንዳንድ ትላልቅ ስሞች ተመልከቱ ከአሌክስ ፈርጉሰን በኋላ እስካሁን ስንት አሰልጣኞችን ተቀየሩ ስለዚህ ፖቸቲንሆም ተመሳሳይ ነገር ይገጥመዋል” ነው ያለው ሊንከር
ጎል ዶት ኮም እንዳስነበበው
✍️ ጀማል ይማሞ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
“ወቅታዊ እና የታመኑ መረጃዎች እንዲደርስዎ የፌስቡክ ገጻችንን ‘Follow’ ያድርጉ።
ሊንኩን ተጭነው ቤተሰብ ይሁኑ፦ 👇
https://www.facebook.com/AMECODessie
“መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ ሼር ያድርጉ – ስለመረጡን እናመሰግናለን!”
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



