የጣሊያኑ ኮሞ ክለብ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ያልተጠበቀ ድንቅ አቋም እያሳየ ይገኛል።
በቀድሞው የአርሰናል አማካይ ሴስክ ፋብሪጋዝ የሚሰለጥነው ክለብ በሴሪያ ኤም ኾነ በቻምፒየንስ ሊጉ ለታላላቅ ክለቦች በቀላሉ እጅ ባለመስጠት በርካታ ድሎችን እያስመዘገበ ነው።
ለዚህ የቡድኑ ጥንካሬ ምሰሶ ከኾኑ ተጫዋቾች መካከል ደግሞ የ23 ዓመቱ አማካይ ማርቲን ባቱሪና በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል።
ክሮሺያዊው አማካይ ካለፈው ዓመት ወዲህ ለክለቡ በ13 ግቦች ተሳትፎ በማድረግ 9 ግቦችን አስቆጥሮ 4 የተቆጠሩ ግቦችን አመቻችቷል።
ከሁሉም በላይ ለፋብሪጋዝ አጨዋወት መሠረት በመኾን በአማካይ ሚና እና የተጋጣሚን እንቅስቃሴ በመቆጣጠር ብሎም በመግታት በኩል ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል።
80 ሚሊዮን ፖውንድ ዋጋ የተቆረጠለትን ይህንኑ ተጫዋች ለማግኘት ቼልሲ እና ማንቸስተር ዩናይትድ ከወዲሁ ከፍተኛ ፉክክር ውስጥ መግባታቸውን ያሁ ስፖርትስ አስነብቧል።
በተለይ ቼልሲ በይፋ ጥያቄ ያቀረበ ሲኾን ማንቸስተር ዩናይትድ በበኩሉ የዝውውር ጊዜው ሲከፈት ወደ እንቅስቃሴ ለመግባት መዘጋጀቱ ተነግሯል።
የተጫዋቹ ፈላጊዎች ግን ሁለቱ ክለቦች ብቻ አይደሉም። ከእንግሊዝ ቶተናም፣ አስቶን ቪላ እና ኒውካስል ዩናይትድ ከጀርመን ደግሞ ባየር ሙኒክ እና አር ቢ ላይፕዚሽ በተለያየ መንገድ ፍላጎታቸውን እየገለጹ መኾናቸውን ዘገባው አመልክቷል።
#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ኅዳር_05_2019_ዓ_ም
በኃይሌ አበራ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



