ደብረ ብርሀን ፡ ህዳር 4/2019 ዓ.ም. (አሚኮ)ማይክል ካሪክን ያሰናበተዉማንችስተር ዩናይትድ ማውሪሲዮ ፖቼቲኖን የክለቡ ቀጣይ ዋና አሰልጣኝ አድርጎ ለመሾም ከስምምነት ደርሷል።
የ54 ዓመቱ አርጀንቲናዊ አሰልጣኝ በክለቡ የሁለት ዓመት ከስድስት ወር የሚያቆየዉን ፊርማ ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል ።
በአሁኑ ወቅት የአሜሪካ ብሔራዊ ቡድንን በኃላፊነት እየመራ የሚገኘው ፖቼቲኖ፣ በቀጣይ ሳምንት ስራውን በይፋ ይረከባል ተብሏል።
ማንችስተር ዩናይትድ የአዲሱን አሰልጣኝ ሹመት ዛሬ ይፋ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።
አሌክስ ፈርጉሰን ማንችስተር ዩናይትድን በጡረታ ከለቀቁ በኋላ በርካታ ቋሚ እና ጊዜያዊ አሰልጣኞች ቢቀያየሩም ክለቡን ዉጤታማ ማድረግ አለመቻላቸዉን ፋብሪዚዮ ሮማኖ አስነብቧል።
ሀብታሙ ዳኛቸዉ



