ዋልያዎቹ ከደቂቃዎች በኋላ ሞዛምቢክን ይገጥማሉ፡፡

0
58

ለ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሦስተኛ ዙር የምድብ ጨዋታውን ዛሬ 10 ሰዓት ላይ ከሞዛምቢክ ጋር ያደርጋል፡፡

እስካሁን ከምድባቸው አንድም ጨዋታ ማሸነፍ ያልቻሉት ዋልያዎቹ የመጀመሪያ ነጥባቸውን ለማሳካት ከሜዳቸው ውጭ ይጫወታሉ፡፡

ጨዋታው በጣም አስፈላጊያችን በመኾኑ ነጥብ ለማግኜትና በውድድሩ ለመቆየት ማድረግ ያለብንን ነገር ሁሉ እናደርጋለን ብለዋል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌ፡፡

የብሔራዊ ቡድኑ አምበል ጋቶች ፓኖም በበኩሉ ከሜዳችን ውጭ የምናደርገው የዛሬው ጨዋታ ከባድ እንደሚሆንብን ብንገምትም ነጥብ ይዘን ለመውጣት በጥሩ ሁኔታ ተዘጋጅተናል ብሏል፡፡

ሀገራችን የምትገኝበትን ይህንኑ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ምድብ 10 ሴኔጋል በ7 ነጥብ ስትመራ ሞዛምቢክ 4፣ሱዳን 3 ነጥብ አላቸው፡፡ኢትዮጵያ ያለምንም ነጥብ የደረጃው ግርጌ ላይ ተቀምጣለች፡፡

ዋልያዎቹ በ4ኛው ዙር የማጣሪያ መርሀ ግብር የዛሬ ተጋጣሚያቸውን ሞዛምቢክን የፊታችን ማክሰኞ በባ/ዳር አለም አቀፍ ስታዲየም ያስተናግዳሉ፡፡

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here